የሚስትነት ተምሳሌት የእናትነት ጥግ | ቤተልሔም አያሌው | Manyazewal Eshetu podcast 15

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 28 мар 2025
  • ወደ ማንያዘዋል እሸቱ ፖድካስት 🎙️ እንኳን ደህና መጡ::
    ይህ ዘወትር እሁድ ወደ እናንተ የሚቀርብ እጅግ በጣም አስተማሪ ፖድካስት ነው::የስኬታማ ሰዎች ታሪክ እና ዕይታ ስንቃኝ አብራችሁን ታደሙ::
    በእያንዳንዱ ክፍል ማንያዘዋል እሸቱ እጅግ በጣም ተፅኖ ፈጣሪ እና ስኬታማ ከሆኑ ሰዎች ጋር ቁጭ ብሎ በጥልቀት ይወያያል::የትም ያልተነገሩ ታሪኮችን ወደ እናንተ ያደርሳል::
    በዚህ በአስራሶስተኛው ክፍል ማንያዘዋል እሸቱ ከ ቤተቴሊሄም አያሌው ጋር ይወያያል::የቤቴሊሄም ታሪክ ልዩ ነው::⁠​⁠ እማርኛ ቻይናዊ ባለቤቷን እያስተማረች::በፍቅሯ ይለክፋል ::እሱ ሀይማኖቱ ገንዘብ ነው::እሷ ደግሞ አክራሪ ክስርስቲያን ነች::​⁠ ምን ተፈጠረ ፖድካስቱ ላይ ጠብቁ::ስለልጅ አስተዳደግ እና ስለቻይና ቆይታዋም አጋርታኛለች::
    የቤቴልሔም ስልክ: +251 95 199 9999
    እስከመጨረሻው በመማር ህይወታችሁን መለውጡን እንዳትረሱ::መልካም ትምህርት:የ

Комментарии •

  • @FirehiwotAsnake-bq7ck
    @FirehiwotAsnake-bq7ck Год назад +30

    በጣም ምርጥ ሴት ናት ክርስቶስ ዉስጧ ያለ.....

  • @mahletEN
    @mahletEN Год назад +32

    የልጅቷ አስተዋይነት እና የመንፈስ እርጋታ እንዳለ ሆኖ ማንያዘዋልም የማዳመጥ ስርአት በጣም ደስ ይላል።

  • @netsanetkifle3928
    @netsanetkifle3928 Год назад +33

    ጎበዝ የኔ ጀገና ለሃይማኖትሽ ክብር መስጠትሽ በራሱ ባልሽ ያከብርሻል ትዳራችሁን እግዚኣብሔር ይባርክ ልጆችሽን ያሳድግልሽ ❤

  • @haimi_hawaz6825
    @haimi_hawaz6825 Год назад +63

    ውይ እንዴት ህይወትን የሚያድስ ታሪክ ነው የተረጋጋ ህይወት እግዚአብሄርን ብቻ ተደግፎ በነብስም በስጋም ልጆችስ ላይ የዘራሽባቸው መንፈሰ ጠንካራነት ብዙ አትራፊነት አንተም አቅራቢው ወንድሜ ዘመንህ ይባረክ ❤❤❤

    • @מקונןאלמיהו-ל5ט
      @מקונןאלמיהו-ל5ט Год назад

      ש'ש מי זזזזזזזזזרזזזזרררר4רר4רר44ר4רררררר4444ררר4א4ר444רר4זשררררר4ררררששששששששששששששששששששששששששששששששששששששששששששששששששששש😅ששששששששששש😅שששש😅ששששששששששששששששששששששששששששש😅שששששששששש😅ששששששששששששששששששששששש ‏‪25:57‬‏

  • @astergeberemichael7237
    @astergeberemichael7237 Год назад +7

    በጣም ፍቅር የሆነችና የተረጋጋች ናት ዮቲዮብ ትክፈት እናሳድግላታለን

  • @marysam9193
    @marysam9193 9 месяцев назад +1

    ህም እንክርዳድ የሚዘራ ኢትዮጵያዊ እንዳለ ሁሉ እንዲህ ምርጥ ስንዴ የሚዘሩ ብርቅየ ስንዴወች ስንዴ የሚዘሩ እንደዚች እንቁ ኢትዮጵያዊትም አለች

  • @bazawitmengesha1147
    @bazawitmengesha1147 Год назад +51

    እንዴትእምትደነቂ ልባም ጎበዝ እናት ; ለሴቶች ምሳሌ የሆንሽ እናት ነሽ !!!
    ከእንቺ ብዙ መማር ይቻላል ተባረኪ 🙏🏾❤️

    • @belayneshchen4039
      @belayneshchen4039 Год назад

      😊

    • @YabsiraAbebe-pn8ws
      @YabsiraAbebe-pn8ws Год назад

      ጥሩ ቆይታ የበረ። ከዚህ የተማርኩትልዩነታችን ዉበት እንዲሆንም ሚያጣላ እንዲሆንም ምናደርገው እኛ ነን።እናመሰግናለን

  • @alembeyene6574
    @alembeyene6574 Год назад +12

    ተባረኪ አንቺንና መላው ቤተስብሽን ፈጣሪ አምላካችን ይጠብቃችሁ እግዚአብሔርን ሳላአከበርሽው ገና ከዚህም በላይ ያደርግልሻል የድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ ካንቺ ጋር ነው አሁንም ቤትሽ በሠላም በፍቅር በበረከት ይሙላ አሜን !!!

  • @ETHIOPIA7500
    @ETHIOPIA7500 Год назад +29

    ዋው--የሚስትነት ተምሳሌት የእናትነት ጥግ - ቤተልሔም አያሌው፤ እጅግ ያተረፍኩበት ፖድካስት ነው - የታመንሽበት ፈጣሪ ዘመንሽን ሁሉ ይባርከው፡፡

  • @abebayeshitila8570
    @abebayeshitila8570 Год назад +46

    Dear, I'm proud to call you 'my friend ' ደስ ይለኛል ..... ስለ ቅንነትሽ፣ ስለ ጥንካሬሽ፣ ሁሌም ስለሚገርመን ስለእግዚአብሔር ነገር ❤

  • @frehiwotmengistu9259
    @frehiwotmengistu9259 Год назад +9

    የረዳሽ እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን።

  • @ethiopiahagerie2679
    @ethiopiahagerie2679 Год назад +39

    ስንቱ ሰባኪ ያልበገረዉን ልቤን ለፀሎት እንድነሳሳ አድርገሽኛል..... ደም ለግሱ ሁሌ የምሰማው ቢሆንም ዛሬ ደም ለመለገስ የወሰንኩበት ቀን ነው ባንቺ ምክንያት 🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @temesgenalemtsehay5354
    @temesgenalemtsehay5354 Год назад +39

    ዋው!እንዴት ደስ የሚል ፕሮግራም ነው ያቀረብክልን ማኔ በጣም እናመሰግናለን።እህታችን በጆሮ ብቻ አይደለም አይኔን ርግብ ለማድረግ እድል የማይሰጥ የመናገር ተሰጥኦ ነው ያላት።እግዚአብሄር ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን!!!አስተማሪ ታሪክ ነው።❤❤❤❤❤

  • @MetiMeti-y2q
    @MetiMeti-y2q Год назад +21

    ትመቸናለች ከ100/100 ሰጥቻታለሁ ልጆቼን እንዴት እናት መሆን እንዳለብኝ ስላስተማርሽኝ ምስጋናዬ ክልብ ነው ማኔ እንተንም ሳላመሰግን አላልፍም ፈጣሪ ይባርክህ ❤❤❤❤❤❤❤

  • @wabilemma
    @wabilemma Год назад +4

    ዋው የእኔ እህት ፀጋውን ያብዛልሽ የሚጠፋ ህይወት የመለስሽ (የባልሽ)ብቻ እግዚአብሔር ባንቺ ሁኖ መልካም ስራ የገለፀብሽ ውብ ሴት ብዙ አስተማሪ ነገር አለሽ ለእግዚአብሔርያለሽ እምነት የሚያስቀና ነውና እኛንም ያንፀን ተባረኪ

  • @የማርያምልጅ-ዘ6ዀ
    @የማርያምልጅ-ዘ6ዀ Год назад +8

    እምትገረም ልዩ የመናገረ ፀጋ ያላት ሴትናት በእውነት እግዚአብሔርፀጋውን ያብዛልሽ❤❤❤

  • @beletetigist9830
    @beletetigist9830 Год назад +1

    ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል ? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቁ እጅግ ይበልጣል ። የባልዋ ልብ ይታመንባታል ። ምርኮም አይጎድልበትም ። ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደግለታለች ክፍም አታደርግም ። ❤

  • @ETL23
    @ETL23 Год назад +8

    ትህትናዋ እወቀቷ ትግስቷ እምነቷ ሁሉን የሰጣት እረጅም ቪዶ እኮ አላዳምጥም ነበር ያንችውስ ቶሎ አለቀብኝ ❤❤እግዚአብሔር የልብሽን መሻት ይፈጽምልሽ ❤❤

  • @abebeadugna212
    @abebeadugna212 Год назад +11

    ሚስት የፈጣሪ ስጦታ ናት የጥቅም ሳይሆን የመንፈስ ትስስር ስትታደል እንዲህ የምሳሌ መገለጫ ትሆናለህ

  • @gebreyesgurmu2733
    @gebreyesgurmu2733 Год назад +2

    ......ለመጠመቅ ፀጉሩን ሲላጭ እግዚአብሔር ልጅህን ከዚያ ድረስ ጠራሀው ወይ አልኩኝ.... የሚለው አገላለፅሽ ለእምነትሽና ለአምላክሽ ያለሽን ከፍ ያለ ክብር የሚያሳይ ነው። ፈጣሪ አብዝቶ ይባርካችሁ!

  • @abebamolla3498
    @abebamolla3498 Год назад +14

    ቢቲዬ!❤ የምታስተላልፈው ነገሮች ሁሉ መሬት ላይ ጠብ የማይል ነው በተለይ ተዋህዶ እምነታችን ያለው ጥንካሬሽ ውስጤን ደስስስስስ አሰኝቶኛል❤❤እኔም እንደቺነው መሆን የምፈልገው

  • @BizuayehuDemissie
    @BizuayehuDemissie Год назад +3

    በስመአብ ሁሌም ባዳምጥሽ አትሰለቺም❤😍🙏

  • @bzuwerqabebe1232
    @bzuwerqabebe1232 Год назад +5

    በእዉነት በምግባር በሃይማኖት አፅናኝ የሚባለዉ በች አየሁ ❤ታድለሽ 👏እግዚአብሔር በዚሁ ያጽናሽ 😍

  • @O_L_D89
    @O_L_D89 Год назад +9

    Omg እሷን ስታዳምጥ ደማሚት እንኳን ቢፈነዳ አትሰማውም። ሴት እንዲህ ስትናገር ትገዛኛለች።ጌታ ከነቤተሰብሽ በዘመን ሁሉ ይባርክሽ❤❤❤

  • @TigistJember
    @TigistJember Год назад +5

    እጅግ በጣም ደስ ትላለች ትችላለች ምርጥ የኦርቶዶክስ ፍሬ ነሽ

  • @embtwodmi5138
    @embtwodmi5138 Год назад +47

    በጣም ነው የምትገርሞው ተመስጬ ነው ያዳመጥካችሁ አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ና ህዝቦቹዋን ይባርክ አሜንንን ❤

    • @manyazewaleshetu
      @manyazewaleshetu  Год назад +5

      Enamesegenalen

    • @birukalehegne
      @birukalehegne Год назад

      via amharic fedel k@@manyazewaleshetu

    • @thesonofsun
      @thesonofsun Год назад

      ማኔ በጣም እናመሰግናለን ቤቲ ያለችህን ብርሽን አንድ ጊዜ አቅርበው እሺ..... ሳያመልጥህ.... ሌላ ጊዜ ደሞ የቤቲን ባለቤት Jack ን
      እወድሃለሁ አከብርሃለሁ
      ግርማ

    • @birhanjommy
      @birhanjommy Год назад

      ልጅትዋ የዳበረ የቋንቋና የመግለፅ ችሎታ አላት። የአማርኛ አስተማሪነትዋን ጠንካራ ጉኗ መሆኑን ተረድታዋለች፣ እኔም እደግፈዋለሁ።

  • @Elsabetnegash-h8o
    @Elsabetnegash-h8o Месяц назад

    አይ፣ማኔ፣ሰላም ፣ነው፣አውን፣ያቀረብከው፣የቻይናዋ፣ሚስት፣በጣም ፣ነው፣ያስደሰተችኝ፣በጣም፣ጎበዝ፣ናት፣አንተም፣ጎበዝነክ፣አደንቅካለሁ፣ማኔ፣ያንተን፣ብሮግራም፣በጣም፣ነው፣የምወደው፣እከታተላለሁ ፣በርታ፣እሺ ፣አድናቂክ፣ነኝ፣

  • @kbb7400
    @kbb7400 Год назад +1

    ምሥጋናዬ በጣም የላቀ ነው እቺን ከሴትም የሴት ቁንጮ ስላቀረብክልን ማንም ወጣት ወላጅ ሊያት ይገባል🙏🏾 የተባረከውን የቻይና ባል ማግኘቷም ጥሩ ነው እንዲህም አይነትም አለ እንድል እረድቶኛል እዚህ አሜሪካ ያሉት ግን ከነጮቹ የባስ ለጥቁር በጣም ንቀት ያሳያሉ ሱቃቸውም ሲገባ ሥራ ፈተው ይከተሉሃል! በርቺ እላለሁ አንተም በርታ አገራችንን ስላም ያድርግልን🙏🏾💚💛❤️

  • @MelakuGirma-z5q
    @MelakuGirma-z5q Год назад +6

    የድንግል ማርያም ልጅ አብዝቶ ይባርክሽ !!!!!!!

  • @yeshiworkmerkebu5872
    @yeshiworkmerkebu5872 Год назад

    ድንቅ ሴት አርዓያ የምትሆን ክርስቲያን እናት!!! እግዚአብሔር በመንገድሽ ሁሉ ይቅደም

  • @achubobasso3002
    @achubobasso3002 Год назад

    እኔ አሁን አንድ ወር እንደሆነው ነው የሚያሳየው የምትገርም እግዚአብሔር በሁሉ ሙሉ ያደረጋት እህት ናት እግዚአብሔር ምንግዜም ስዎች አሉ እግዚአብሔር ይመስገን እምነትሽ በጣም ያኮራል እግዚአብሔር ይባርክህ ከነቤተሰብሽ።

  • @SelasTesfaye
    @SelasTesfaye Год назад +1

    አውነት እውነት አደበትሽ ይባረክ ድንቅ ነሽ በዚች ደቂቃ ውስጥ ብዙ ነገር አስተማርሽኝ ተባረኪ ዘመንሽ ይባረክ

  • @samuelts7461
    @samuelts7461 Год назад +23

    በጣም ደስ የሚል የመደመጥ ለዛ አለሽ እግዚአብሔር ህይወትሽን ሁሉ ይባርክልሽ . . .
    ማኔ ' ዘይገርም ' የሆነች ሴት ስለጋበዝክልን እናመሰግናለን . . .

  • @Mebadt2016
    @Mebadt2016 Год назад +3

    በጣም የምትገርሚ ኢትዮጵያዊ እህት ብዙ ኢትዮጵያውያን ሌላ ዘጋ ሲያገቡ እንደኩራት ከነ ዝርክርክነታቸው ተቀብለው ምድርን መረገጥ ለሚፀየፉ ምስለ እትዮ---- ትልቅ ትምህርት

  • @marysam9193
    @marysam9193 9 месяцев назад

    ይች ሴት ትክክለኛ ኢትዮጵያን የልቧ ንግስት የማንነቷ መሰረት መሆኗን በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የተገበረች እንቁ ናት ባለቤቷ ቻይንየም ፈጣሪ የመረጠዉ የተዋህዶ እንቁ ነዉ!!!

  • @sabusaa5641
    @sabusaa5641 Год назад +4

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ወይኔ ታድላ ብሰማት ብሰማት የማትጠገብ ልጅ እግዚአብሔር ጨምሮ ይስጥሽ ፀጋ ነው ይሄ እራሱ

  • @Azeb-ru1rf
    @Azeb-ru1rf Год назад +3

    ደስ ስትል #ቻይናው አፈሰ

  • @marysam9193
    @marysam9193 9 месяцев назад

    ዋዉ ኢትይጵያ የራባት እንቁና ዋጋ የከፈሉላትን ልጆቿን የሚያመሰግንላትና አለሁ የሚላቸዉ የሚላቸዉ ሰዉ ማጣት ነዉ ተመስገን እምየ በዚህ ሁሉ መካራሽ ዉስጥ እንዲህ ዋጋ የከፈሉልሽን የሚያስቡ የተካደዉ ማንነትሽን ወደ ነበረዉ ማንነትሽ ለመመለስ አንዲህ የመጥሩ አሉሽ ደስ ይበሉሽ እማማ !!

  • @ApramMan
    @ApramMan 7 месяцев назад

    ዋዉ እዉነትም የእናትነት ጥግ ጀግና ሴት ነሺ ለሀይማኖትሽ ያለሽ ክብርና አቋም በጣም የሚገርም ና ለኛ ለወጣቶች የሚያበረታታ ነዉ አንደበተ ርእቱ እግዚአብሔር ትዳርሽንና ልጆችሽን ይባርክ.....ማንየም እግዚአብሔር ያክብርህ እንደነዚህ አይነት እንቁ ሰወችን እየጋበዝክ ብዙ ነገሮችን እንድንማር ስላደረክ....ቀጥልበት በርታ...

  • @HelenG-r4e
    @HelenG-r4e Год назад

    ደም መለገሰ እወድ ነበር ግን ለመጀመሪያ ሰለግስ ደም ነርሳ ከመጠን በላይ ወሰደብኛ አሳምማኛለች ከዛ ብኃላ ሁሌ ነው እምበስጨው❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @YesharegTeshome-e7j
    @YesharegTeshome-e7j Год назад +5

    እውነት ሽንት ቤት እያጠብኩ ነበርና ትመችኝለች በሉ ስትል ጎንት አውልቄ ነው የምፅፍላት እውነት ትልቅ ትምህርት ግን እንዲህ ባዶ ነኝ ነው ያልኩት እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ እኔ አንደኛ ነኝ በጉጉት ስብስክራይብ አድራጊዋ

  • @SakiraSkira-rv8sr
    @SakiraSkira-rv8sr Год назад +5

    ቤቲዬ የኔ ቆንጆ እግዚአብሔር አብልጦ ይባርክሽ ፀጋውን ያብዛልሽ ከነ ሙሉ ቤተሰብሽ ተባረኪልኝ 😇😇😇

  • @ሰደተይልሂወትኮይንለይ

    አርጋታዋ ደሰሰሰ ስል ተባረኪ የልብሽ መሻት ጌታ ይፈፅምልሽ❤

  • @samsonalemu8536
    @samsonalemu8536 Год назад +1

    እግዚአብሔር ይባርክሽ የምን ሴቶች ብቻ እኛም ወንዶች እንወድሻለን እናደንቅሻለን።

  • @TilahunGetachew-ks9ee
    @TilahunGetachew-ks9ee 4 месяца назад +1

    በጣም ትምህርት ሰጪ ቃለምልልስ ነው። በርቺ።

  • @YemarwehatilahunYemarwehatilah
    @YemarwehatilahunYemarwehatilah Год назад +1

    እኔ በእውነት በምትጠየቀው ጥያቄ የምትሰጠው መልስ በጣም አስደስቶኛል እግዚአብሔር አሁንም እውቀትሽን ያብዛልሽ❤❤

  • @aamm1852
    @aamm1852 Год назад

    የእውነት በጣም ተመስጭ ነው የሰማሁት በጣም እምትገርሚ ድንቅ ሴት ነሽ ትህትናሽ ኣወራርሽ የቃላት ኣጠቃቀምሽ በቃ ሁለመናሽ ደስስ ይላል ሶ እኔም እንድንቺ ረጋ ያለ ፋሚሊ እንዲኖረኝ ምኛቴ ነው ይሄን ኾሜንት ምታነቡ ሰዎች የልባቹን መሻት ይፈፅምላቹ እግዚአብሔር የምንፈልገው ሳይሆን የሚያስፈልገን ያጠን ኣሜን!

  • @senaitbogale277
    @senaitbogale277 Год назад +11

    ወንድሜ በመጀመሪያ ፈጣሪ ይባርክህ ያቀረብክልንን ውዷን እህታችንንም ዘመኗ የተባረከ ይሁንልን ታሪካዊ ሴት ነች ልጆቿን ፈጣሪ እቅፍ ድግፍ አድርጎ እንደእናታቸው ፈጣሪን አጥብቀው የሚይዙ ለቀጠይ ትውልድም መንፈሳዊ ትምህርት የሚያደርሱልን እንዲሆኑልን እፀልያለሁ::

  • @abelabi6782
    @abelabi6782 Год назад +14

    I have a child and I have learned a lot from her treatment with her children thank you very much🇪🇷🇸🇪

  • @betelhemadamseged5744
    @betelhemadamseged5744 5 дней назад

    Beti betam teleweteshal temerebeshalew tebareki😊

  • @kokebendale8918
    @kokebendale8918 Год назад +3

    በጣም ትልቅ ቦታ ያለሽ ነሽ እግዚአብሔር የልብሽን ያሳካልሽ።

  • @radethuae9724
    @radethuae9724 Год назад

    ጎበዝ ሴት በጣም ጠንካራ ነሽ ከምንም በላይ በሀይማኖትሽ ጠንካራ ስለሆንሽ እግዚአብሔር ይጠብቅሽ ከነቤተሰቦችሽ ✝️❤️⛪️🙏

  • @bezawitmideksa4665
    @bezawitmideksa4665 Год назад +1

    በጣም ድንቅ ሴት ፀጋውን ያብዛልሽ

  • @SingitanOromiya
    @SingitanOromiya Год назад

    አረ ምን አይነት የምስብ ለዛ ያለዉ አንደበት ነዉ መድኃኒዓለም ያደለሽ፤ አረ በጣም ነዉ የደነቀኝ መድኃኒዓለም ፀጋዉን ይጨምርልሽ

  • @KalkedanAdugha
    @KalkedanAdugha Год назад +2

    በጣም የተረጋጋሽ ሴት አስተዋይ ትልቅ ሰው ነሽ ለብዙዎች አርአያ ነሽ የእግዚአብሔር ጥበቃ ይብዛልሽ ❤❤❤

  • @TesfayeWube-j8q
    @TesfayeWube-j8q 9 месяцев назад

    EGZIABHER YMESGEN BETAM DES YEMIL WUYIYET NEW❤❤❤❤❤❤❤

  • @SelamawitTeddy
    @SelamawitTeddy Год назад +1

    በጣም ወድጃታለው ተመችታኛለች ጥሩ አስተሳሰብ አላት

  • @messeretbekele2888
    @messeretbekele2888 Год назад +2

    በጣም ብዙ ትምህርተ ተምሬአለሁ እግዚአብሔር ይባርክሽ

  • @alemtsehaysesaysisay7144
    @alemtsehaysesaysisay7144 Год назад +3

    ውው ተመስጨ ነው የሰማውት ማኔ ከፕራግራሞችህ የሚመቸኚ እሄ ነው ግን የዮጋውን ነገር ብታስብበት እውነት የቡዲህዝም የሰይጣን አምልኮ ባትከተል ደስ ይለኛል በተረፈ በርቱ❤

  • @assegdechdejene3500
    @assegdechdejene3500 Год назад +1

    ፐ ምርጥ እናት ቀጣዩ ጊዜሽን እግዚአብሔር ይባርከው

  • @nunubelete8142
    @nunubelete8142 Год назад +1

    እህቴ በጣም የተረጋጋ መንፈስ አለሽ ካንቺ አልፎ ሌላው የምታጋቤው በጣም ተመስጬ ነው ያየሁሽ ፈጣሪ ይመስገን ንግግሮችሽ ሁሉ በተመረጡ ቃላት የተሞሉ ጉራማይሌ ያልሆኑ ፅድት ያሉ አስተማሪዎች ናቸው እራስሽን የሆንሽ ቅን ሰው ሆነሽ ስላገኘሁሽ ላይሽ ልከተልሽ ፍቃደኛ ነኝ ። ማኔ ግን ወይ አማሪኛ አውራን ወይም እንግሊዝኛውን ምረጥ የአንተን አነጋገር ዘይቤ የየሚሰሙ ታዳጊዎች እንዳይሰናከሉ እሰጋለሁ በቀላሉ ተመቸኝን ለሰው አትልም ወንበሩ ፣ አልጋው ፣ ጫማውን ነው ተመቸን የሚባለው 😢 አዝናለሁ ወደፌት አገር ተረካቤው ማነው ? ወጣቱ አጎል እየሆነ ነው አንተ ከነሱ ተሽለህ ስትገኝ ነው ወዳንተ የሚሳቡት እህቴ ግን በርቺ የሚገርም ስብእና ነው ያለሽ 💕🙏💕 💚💛❤ 🤗💪

  • @haregabebe1728
    @haregabebe1728 Год назад +3

    ማኔ እናመሰግናለን አክባሪህ ነኝ መሰረት መብራቴን እባክህ አቅርብልን❤❤❤

  • @yeshiworkalebign-p1q
    @yeshiworkalebign-p1q Год назад +1

    እንዴት ደስ የሚል ፕሮግራም ነው ያቀረብክልን ማኔ በጣም እናመሰግናለን..

  • @azaoude
    @azaoude 10 месяцев назад

    ምርጥ አስተማሪ ውይይት ነበር:: ተባረኩ:: ልጆቹ የቻይናዊ አባታቸውንም አገር እያወቁና እያከበሩ ቢያድጉ የአለም ዜጋ በመሆን ድንበር ተሻጋሪ ማንነት ይኖራቸው ነበር:: የሁለት አገር ዜግነት መያዝ: አለምን ማወቅ: እድለኝነት ነው:: በርቺ::

  • @frehiwotlemma4437
    @frehiwotlemma4437 Год назад +2

    አቤት እርጋታሽ ደስ ሲል ቀሪውን ዘመንሽን ይባርክልሽ የልብሽን መሻት ይፈጽምልሽ ማኔም በርታልን እንደዚህ አስተማሪ የሆነ ፕሮግራም ነው ያቀረብከው♥♥♥♥♥

  • @dejenedesalegn2055
    @dejenedesalegn2055 Год назад +3

    እግዚአብሔር ይስጥልኝ ፣መልካም ቆይታ ነበር ፣በዚሁም ትልቅ የሰብዕና ግንባታ ዕውቀትን አግኝቼበታለሁና እግዚአብሔር ይስጥልኝ ።እግዚአብሔር የጀመርሽውን ያሰብሽውን መልካም ነገሮች ሁሉ ይባርክልሽ ዘንድ ፀሎቴ ነው።አድማጭ የነበርንውን እንዳንቺ ትልቅ ልብና ሕልም ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር ፍቃዱ ይሁንልን።

  • @s0lomon150
    @s0lomon150 Год назад

    ፀጋ የበዛልሽ ሤት ነሽ ተደምጠሽ አትጠገቢም ኢትዮጵያዊት በመሆንሽ ኩራት ይሰማኛል ቀሪ ዘመንሽ ይባረክ

  • @melatmezgebe
    @melatmezgebe Год назад +2

    በጣም የምትገርም በጥበብ የተሞላች ሴት ናት ካንቺ ብዙ ነገር እንጠብቃለን🙏❤

  • @sabaalemseged
    @sabaalemseged 17 дней назад

    ❤❤❤ዋዉ በጣም ነዉ የትመቸችኝ ሁለታቹም ትባርኩ🙏🙏🙏

  • @BetelhemBirhanu-o8s
    @BetelhemBirhanu-o8s Месяц назад

    የእኔ ልዕልት እመብርሃን አትለይሽ ትቁምልሽ ከነ ቤተሰብሽ❤❤❤

  • @tinyohannes5282
    @tinyohannes5282 Год назад +3

    ለኔም መደሀኒያለም ያደረገልኝ የተለዬ ነው

  • @ጌታዬንፁህልብስጠኝ

    ብርክ በይ የኔ ቆንጆ ቀሲስ አሸናፊ ገማርይምማ ጥልቅ ይህይወት የሚያሲዝ መምህር ነው እግዚአብሔር ይባርከው እብልክችው ዲያቆን አሸናፊ መኮንንምአድምጡት ምጡቅ አይምሮ እና አስተምሮ ያለው ነው ማንዬ ተባረክ የኔ ጎበዝ ብርክ በል

  • @getayakalalene-tq4js
    @getayakalalene-tq4js Год назад

    በጣም የምትገርም አረዳድ ያላት እና ንግግሯም በማር የታሸ ንግግር የምትናገር ግሩም ሴት ናት ሌላ ጊዜም ቃለ መጠይቅ አድርግላት፡፡

  • @wobebele579
    @wobebele579 Год назад +4

    ከወ/ሮ ቤቲ በጣም ጥሩ የእምነት የትዳር የስነስርአት የአገር ፍቅር የደም መስጠት ጥቅም..የቤተሰብ ፍቅር....ተምሬባታለሁ አመሰግናተለሁ።እናንተነም ጭምር ማኔ።

  • @berketfantahun727
    @berketfantahun727 Год назад

    ማኔ በጣም ጀግና ነህ ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቅህ ግን ካንተ ገና ብዙ ነገር እጠብቃለው ብሮ ወደፊት ወደፊት

  • @kokebendale8918
    @kokebendale8918 Год назад +1

    ትክክለኛ አባባል ቤተክርስትያንን እንስማ ይህ ዋናው ነው።

  • @ABANSHMM9
    @ABANSHMM9 11 месяцев назад

    ዋው የእውነት የሴት ምሳሌ ናት በጣም ነው የወደድሗት ብዙ ተምሪያለሁ

  • @sebli5075
    @sebli5075 Год назад +1

    ምን አይነት ጎበዝ ሴት ነሽ የምር ቀናሁብሽ ትለዪአለሽ እናመሰግናለን ማኔ

  • @zerfiedejene8802
    @zerfiedejene8802 Год назад +1

    በጣም ተመስጬ አዳመጥኳት እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  • @omersenayt905
    @omersenayt905 Год назад +1

    አይገርምሽም ይህን ፕሮግራም የመጀመሪያ ጊዜ ስከታተል ጠልቼው ሳይሆ በቃ የሆነ ግር ግር ሁካታ ጫጫታ ስለማይመቸኝ እንደዛ ስለሚመስለኝ ትኩረት የለኝም ነበር አነጋገርሽ ይስባል ያስተምራልም ተባረኪ ልጆችሽ ይባረኩልሽ የበለጠ ሀይማኖቴን እንድወድ ስላረግሽኝ እያለቀስኩ ነው የተከታተልኩሽ

  • @kblovers9284
    @kblovers9284 Год назад +2

    ዋውው ከንኣንን ጋር የሰራሺው ቪድዮ ኣይቼ ኣስታወስኩሽ በጣም ነበር ያስለቀሰኝ ልጁም ከንኣንም ያንቺም ሀሳብ በጣም ገራሚ ሴት ነሽ በዩቱፕ ነይልን በናትሽ 😢❤

  • @ruye15
    @ruye15 Год назад +2

    እግዚአብሔር ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን!!! በጣም ጥሩ ትምህርት ነው የሰጠሽን፡፡

  • @aschebogala7673
    @aschebogala7673 Год назад

    በእውነት የሴትነት ጥግ ከውቀት ጋር ያጎናፀፋት ምርጥ ሴት ዘርሽ ይባረክ እግዚአቤሔር አምላክ መጨርሺያችውን ያሳምርላችው በስስት በፍቅር ነው ያዳመጥኩሽ እህቴ ሠላምሽ ይብዛልኝ

  • @mesiGodolyas
    @mesiGodolyas Год назад

    ጀግኒት በርቺ በብዙ እንጠብቅሻለን

  • @emuyahya9351
    @emuyahya9351 Год назад +1

    ረጋ ያለች ሴት ቁምነገር አዘል ንግግር እዴት ብዙሰው እደሚጠቅም የተናገርሹ እኔ ራሴ ለእረፍት ፖላን አሳሺን እዚው ለደን ተቀምጠን ካብረጅ ወስጃቸው አላቅም የቤት ስራ ሰጠሽን ጎበዝ እናት ❤❤ አመሰግናለሁ

  • @bereketbemenet503
    @bereketbemenet503 Год назад +1

    በጣም የተደሰትኩበት ዉይይት የሰፈሬልጅ ቤቲ በጣም ሀይል አቅም አለሽ አውጪው በናትሽ በተለይ በሀይማኖትና በስነ ምግባር የገነባ ማንነት ግሩምነበር በርቺ 🌹 😍 😘

  • @Bizuayehu-l2w
    @Bizuayehu-l2w Год назад

    እኔ እንጃ ምን ብዬ ልጀምር ከአይምሮ በላይ ነሽ :: እርጋታሽ ድርብብ ያልሽ አንደበይሽ አገላለፅሽ በእውነት ይለያል እህቴ እንደ አንቺ ያለውን ድንቅ ሴቶችን ያብዛልን :: ተባረኪልኝ ::

  • @genetmelesse7569
    @genetmelesse7569 Год назад +19

    Very educational interview.
    Ethiopia needs a leader who
    Can guide her. Also it is not easy to compare Ethiopia with China, they have paid a price to get where they are now. We will get there.
    With the help of God!!!🙏🏾

  • @thesonofsun
    @thesonofsun Год назад +2

    ውድ እህቴ ቤቲ ብዙ የምታቀርቢው የህይወት ገጠመኞች እንዳሉሽ ከድሮ የልጅነሽ ቀልዶችሽ አውቃለሁ: ደስስስ ብሎኝ እየነዳሁ አገር በሚረብሽ ድምፅ አደመጥኩሽ::የራስሽን አይደለም የሁሉንም ሰው/የቤተሰብና ጉዋደኞችን! ዘርዝረሽ ብትፅፊ መፅሀፍ ይሆናል እንገዛሻለን:: say hi to Jack and the kids
    I miss you

  • @tsedeygashaw4426
    @tsedeygashaw4426 Год назад +3

    Wow she is amazing 👏 I like her 😍

  • @ሙሉወለተማርያምነኝየድንግ

    እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ምትገርም እህት መድኃኔዓለም ይባርክሽ ከኔ በተስቦችሽ እግዚአብሔር ይስጥልን ደስ ምል ትምህርት ጸጋውን ያብዛልሽ በተለይ በሃይማኖትሽ ያለሽ ፍቅር ጨምሮ ይርጥሽ በቤቱ ያኑርሽ🤲🥰🥰🥰

  • @SerkalemWorku-n2i
    @SerkalemWorku-n2i 2 месяца назад

    በጣም ደስ የምትይ ነሽ ከናትሽ የወረሽው ውርስ በጣም ግሩም ነው
    ግን ተተኝቶ ወይም ተቀምጦ አይፀለይም

  • @kaltes9766
    @kaltes9766 Год назад

    ዛሬ ምርጥ የ ፆም ምግብ የሆነች፡ አንደበቷ ጣፋጭ፡ በእርጋታ የተሞላ አነጋገር ያላት፡ ጥሩ ይዘት ያለው ቃለ-መጠይቅ፡ጥሩ የልጅ አስተዳደግ ልምድ ስላካፈልከን አመሰግናለሁ። ቢሆንም ቅሉ ስለ ዲሞክራሲ ስታወሩ "አእምሮአቸው የታሰረ ነው" ያላችሁት አልተመቸኝም። ሰው ገደብ ካልተደረገበት ከእንስሳ የከፋ ነው። ደሞም እንዲያ በማድረጋቸው ዲሞክራሲ በሚል ሽፋን ከብዙ የምእራባውያን ሴራ እራሳቸውን አድነዋል። Creativity ቻይና ውስጥ በጣም ትልቅ እድል አለው። በተለይ ከ2012 Xi Jinping ከመጣ ወዲህ ለ Creativity ትልቅ እድል ከፍቷል ። ጌታቸው ረዳን አልሰማሽው መሰለኝ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲዖል ድረስ እንደሚወርድ😅😅😅

  • @AbebaKebede-dy8ls
    @AbebaKebede-dy8ls 7 дней назад

    ለእኔ ተመችታኛለች

  • @nigusumesele166
    @nigusumesele166 Год назад

    ገራሚ ሴት! በእውነት ሃሳብሽን መድኃኔአለም ያስፈጽምሽ።

  • @selam801
    @selam801 Год назад +3

    ዋው እንዴት ደሰ የሚል ፕሮግራም ነው ያቀረብክልን ማኔ እናመሰግናለን እውነት በጣም ብልህ ሴት ናት💙

  • @selamawithailegebrail9825
    @selamawithailegebrail9825 Год назад

    በጣም የምትደነቂ ግሩም ሴት ነሽ እግዚአብሄር ያሰብሽውንና እሱ ደግሞ ሊሰራ የፈለገውን
    በአንቺ ሆኖ እንድናይ ይፍቀድልሽ ተባረኪ

  • @ethiogondarmedia8706
    @ethiogondarmedia8706 Год назад +3

    የኔ ቆንጆ በጣም ነው ደስ የምትይው እግዚአብሔር እንኳን መረጠሽ በቤቱ ያጽናልሽ

  • @Mekedsmekeds-b8z
    @Mekedsmekeds-b8z Год назад

    በጣም ተምችታቹናል 10qso mache ማኔ🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @KidestJk
    @KidestJk 8 месяцев назад

    በጣም ነው የወደድኩሽ የኔ ውድ ዘርሽ ይባረክልሽ